በUNHCR፣( የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ) ወደሚተዳደረው ‘እገዛ’ ገጽ እንኳን በደህና መጡ። በ UNHCR ሊቢያ የተመዘገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች በUNHCR እና በአጋሮቹ ከሚሰጡት አንዳንድ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
ጠቃሚ ምክር፡ ሁሉንም ያሉትን ይዘቶች ለማሰስ ከ UNHCR አርማ ቀጥሎ ከላይ በግራ ጥግ በኩል ያለውን የ’ Menu’ ቁልፍን ይጠቀሙ::
በዚህ ገጽ ላይ ስለሚከተሉት ጉዳዮች መረጃ ያገኛሉ፡-
- UNHCR ሊብያን በተመለከተ እና ከመስሪያቤቱ ጋር እንዴት መገናኘት እንደሚችሉ
- አስፈላጊ አድራሻዎች እና የስልክ መስመሮች
- በUNHCR እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል
- ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም እና ጊዚያዊ መቆያ በረራዎች ስለማድረግ
- እርዳታ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል
- የ ስነ-ስርዓት ጉድለትን ሪፖርት ስለማድረግ ወይም ቅሬታን ስለማቅረብ
እባክዎን በ UNHCR የሚሰጡ ሁሉም አገልግሎቶች፣ ምዝገባን ጨምሮ፣ በነጻ እንደሚሰጡ ይወቁ።